Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐጌ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ‘ይህን ቤት በቀድሞ ክብሩ ሳለ ያየ ከመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ ምን መስሎ ይታያችኋል? ይህ በፊታችሁ ምንም እንዳይደለ የሚቈጠር አይደለምን?’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምንም አይደለምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “የዚህ ቤተ መቅደስ የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደ ነበረ ያየ ሰው በእናንተ መካከል አለን? ዛሬስ እንዴት ሆኖ ታዩታላችሁ? ይህ በእናንተ ዘንድ እንደሌለ የሚቈጠር አይደለምን?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?

See the chapter Copy




ሐጌ 2:3
8 Cross References  

የፊ​ተ​ኛ​ውን ቤት ያዩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የሆኑ ብዙ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች ግን ይህ መቅ​ደስ በፊ​ታ​ቸው በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ያለ​ቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም እየ​ዘ​መሩ በደ​ስታ ይጮኹ ነበር፤


የክ​ብ​ሩ​ንም ጌጥ ወደ ትዕ​ቢት ለወጡ፤ የር​ኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ምስ​ሎች አደ​ረ​ጉ​ባት፤ ስለ​ዚህ እኔ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አድ​ር​ጌ​አ​ታ​ለሁ።


ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ዳዊ​ትም፥ “ልጄ ሰሎ​ሞን ታና​ሽና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሠ​ራው ቤት እጅግ ማለ​ፊ​ያና በሀ​ገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እን​ዲ​ጠራ ይሆን ዘንድ ይገ​ባል፤ ስለ​ዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ለ​ታ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ሳይ​ሞት አስ​ቀ​ድሞ ብዙ አዘ​ጋጀ።


ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ እርስ በር​ሳ​ቸው ያስ​ተ​ዛ​ዝሉ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በሩ በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ።


የተ​ቀ​ደሱ ከተ​ሞ​ችህ ምድረ በዳ ሆነ​ዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውድማ ሆና​ለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements