Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐጌ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፣ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፣ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ሐጌ እንዲህ አለ፤ “ ‘ይህ ሕዝብና ይህ ወገንም በፊቴ እንደዚሁ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የእጃቸው ሥራና የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።’

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል ጌታ፤ የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ ያቀረቡትም ርኩስ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሐጌም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ በሙሉ እንደዚያው ነው፤ ስለዚህ ሥራቸውና የሚያቀርቡት ቊርባን የረከሰ ነው” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፥ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው።

See the chapter Copy




ሐጌ 2:14
11 Cross References  

ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


ለስድብ በልብ አለመቸኮል ታላቅ ዕውቀት ነው የኃጥኣንም ብርሃናቸው ኀጢአት ነው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ይን ጠጅን ቍር​ባን አያ​ቀ​ር​ቡም፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ውም፤ እንደ ኀዘ​ንም እን​ጀራ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ይረ​ክ​ሳል፤ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውም ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ይሆ​ናል እንጂ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ገ​ባም።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements