Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከወ​ይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ ዕራ​ቁ​ቱን ሆነ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዕለታት አንድ ቀን ከወይን ጠጁም ጠጣ፥ ሰከረም፥ በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ተኛ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዕለታት አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ ልብሱንም አውልቆ ራቊቱን በድንኳን ውስጥ ተኛ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከወይን ጠጁም ጠጣና ስከረ በድንኳኑም ውስጥ ዕርቁቱን ሆነ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 9:21
13 Cross References  

ለተሳዳቢና ለሰካራም ወይን ክፉ ነው፥ ጽዋውንም መላልሶ የሚጨልጥ ጠቢብ አይደለም፥ እንደዚህ ያለ አላዋቂም ሁሉ አንድ ይሆናል።


ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤


አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።


አሁ​ንም ያ ቆሜ​አ​ለሁ ብሎ በራሱ የሚ​ታ​መን ሰው እርሱ እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ ይጠ​ን​ቀቅ።


በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።


ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።


ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፤ ወይ​ንም ተከለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements