Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ውም ሁሉ ዳግ​መኛ በጥ​ፋት ውኃ አይ​ጠ​ፋም፤ ምድ​ር​ንም ለማ​ጥ​ፋት ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃ አይ​ሆ​ንም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚህም በገባሁላችሁ ቃል ኪዳን መሠረት፥ ከእንግዲህ ወዲህ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ በጥፋት ውሃ ከቶ አይደመሰሱም፤ ምድርም ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አትጠፋም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ቃል ኪዳንርንም ለእናንተ አቆማልሁ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኝ በጥፋት ውኃ አይጠፉም ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኅ አይሆንም።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 9:11
8 Cross References  

ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስ​ክር ነው፤ ቀድሞ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ምድ​ርን እን​ዳ​ል​ቈ​ጣት እንደ ማልሁ፥


ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤


አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።


ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል።


በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ሕያው ነፍስ ባለ​ውም ሥጋ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ው​ንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃን አላ​መ​ጣም።


መከ​ራ​ህ​ንም እን​ዳ​ለፈ ማዕ​በል ትረ​ሳ​ለህ፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ አት​ደ​ነ​ግ​ጥም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements