Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ወደ መር​ከ​ብም አንተ ልጆ​ች​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ትገ​ባ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከአንተ ጋራ ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋራ ወደ መርከቧ ትገባላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ይዘህ ወደ መርከቡ ትገባለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ ግቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 6:18
11 Cross References  

ኖኅም ስለ​ማ​ይ​ታ​የው ነገር የነ​ገ​ሩ​ትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡ​ንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መር​ከ​ብን ሠራ፤ በዚ​ህም ዓለ​ምን አስ​ፈ​ረ​ደ​በት፤ በእ​ም​ነ​ትም የሚ​ገ​ኘ​ውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ።


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ና፤ ወደ ቤት​ህም ግባ፤ ደጅ​ህን በኋ​ላህ ዝጋ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸ​ሸግ።


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ኖኅን አለው፥ “አንተ ቤተ​ሰ​ቦ​ች​ህን ሁሉ ይዘህ ወደ መር​ከብ ግባ፤ በዚህ ትው​ልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይ​ች​ሃ​ለ​ሁና።


ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”


“እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል አጸ​ና​ለሁ፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም አባት ትሆ​ና​ለህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements