Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 50:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​አ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ እኔን በእግዚአብሔር ቦታ ማን አስቀመጠኝ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዮሴፍም አላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን ነኝ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ነገር ግን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የምሆን አይደለሁም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ዮሴፍም አላቸው፦ አትፍሩ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 50:19
11 Cross References  

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ራሳ​ችሁ አት​በ​ቀሉ፤ ቍጣን አሳ​ል​ፏት፥ “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔ ብድ​ራ​ትን እከ​ፍ​ላ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ተብሎ ተጽ​ፎ​አ​ልና።


አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና።


ያዕ​ቆ​ብም፥ “የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽን ፍሬ የም​ከ​ለ​ክ​ልሽ እኔ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝን?” ብሎ ራሔ​ልን ተቈ​ጣት።


“እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔም ብድ​ራ​ትን እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ያለ​ውን እና​ው​ቀ​ዋ​ለ​ንና፤ ዳግ​መ​ኛም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ይፈ​ር​ዳል።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።


በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።


ዮሴ​ፍም ይህን ሲሉት አለ​ቀሰ። ወን​ድ​ሞቹ ደግሞ መጡ፤ “እነሆ፥ እኛ ለአ​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን” አሉት።


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements