Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ስላ​ሰ​ኘው አል​ተ​ገ​ኘም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው​ሮ​ታ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ፥ እግዚአብሔር ወስዶታልና፥ ሄኖክ አልተገኘም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ይህን ያኽል ዘመን የኖረውም የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ነበር፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ወሰደው አልተገኘም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 5:24
19 Cross References  

ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


ሄኖ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው፤ ሄኖ​ክም ማቱ​ሳ​ላን ከወ​ለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወን​ዶ​ች​ንም፥ ሴቶ​ች​ንም ወለደ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ በገ​ነት ከእኔ ጋር ትሆ​ና​ለህ።”


ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።


አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”


ሮቤ​ልም ወደ ወን​ድ​ሞቹ ተመ​ልሶ፥ “ብላ​ቴ​ናው በጕ​ድ​ጓድ የለም፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች።


ከዚ​ህም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኤል​ያ​ስን በዐ​ውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚ​ያ​ወ​ጣው ጊዜ ኤል​ያ​ስና ኤል​ሳዕ ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።


“ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና።”


ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኀጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል፤” ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።


ሄኖ​ክም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዓመት ሆነ።


ማቱ​ሳ​ላም መቶ ሰማ​ንያ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜ​ሕ​ንም ወለደ፤


የኖኅ ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ኖኅም በት​ው​ልዱ ጻድቅ፥ ፍጹ​ምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው።


እር​ሱም አለኝ፦ አካ​ሄ​ዴን በፊቱ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከአ​ንተ ጋር ይል​ካል። መን​ገ​ድ​ህ​ንም ያቀ​ናል፤ ለል​ጄም ከወ​ገ​ኖች ከአ​ባ​ቴም ቤት ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤


ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው።


በመ​ከ​ራህ ቀን ትጠ​ራ​ኛ​ለህ አድ​ን​ህ​ማ​ለሁ፥ አን​ተም ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።


ኤል​ሳ​ዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ኀይ​ላ​ቸ​ውና ጽን​ዓ​ቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚ​ያም ወዲያ ዳግ​መኛ አላ​የ​ውም፤ ልብ​ሱ​ንም ይዞ ከሁ​ለት ቀደ​ደው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements