Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 49:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አህ​ያ​ይ​ቱን በወ​ይን ግንድ ያስ​ራል፤ የአ​ህ​ያ​ይ​ቱ​ንም ግል​ገል በወ​ይን ሐረግ፤ ልብ​ሱን በወ​ይን ያጥ​ባል፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ው​ንም በዘ​ለ​ላው ደም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ፥ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አህያውን በወይን ግንድ ላይ፥ ውርንጫውን በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፥ መጐናጸፊያውን እንደ ደም በቀላ የወይን ጭማቂ ያጥባል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል የአህያይቱንም ግልግል በወይን አረግ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 49:11
15 Cross References  

እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ተራ​ሮች ማርን ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ችም ወተ​ትን ያፈ​ስ​ሳሉ፤ በይ​ሁ​ዳም ያሉት ፈፋ​ዎች ሁሉ ውኃን ያጐ​ር​ፋሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ምንጭ ትፈ​ል​ቃ​ለች፤ የሰ​ኪ​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ታጠ​ጣ​ለች።


የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።


በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።


ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን፥ ወይ​ራና ማር ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም ነው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ና​ች​ኋል ብሎ ያታ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና አት​ስ​ሙት።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።


ዐይ​ኖቹ ከወ​ይን ይልቅ ደስ ያሰ​ኛሉ፤ ጥር​ሱም ከወ​ተት ይልቅ ነጭ ነው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መል​ካ​ምና ሰፊ ምድር፥ ከሜ​ዳና ከተ​ራ​ሮች የሚ​መ​ነጩ የውኃ ጅረ​ቶ​ችና ፈሳ​ሾ​ችም ወዳ​ሉ​ባት ምድር፥


ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥


በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።


“እነሆ፥ እን​ዲህ ያለ ወራት ይመ​ጣ​ልን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እርሻ ከአ​ጨዳ ጋር፥ ዘርም ከእ​ሸት ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ከተ​ራ​ሮ​ችም ማር ይፈ​ስ​ሳል፤ ኮረ​ብ​ታ​ውም ይለ​መ​ል​ማል።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements