Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 48:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም፤ በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዮሴፍም አባቱን፦ “አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኩሩ ይህ ነውና፥ ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “አባቴ ሆይ፥ እንደዚህ አይደለም፤ በኲሩ ይህኛው ስለ ሆነ ቀኝ እጅህን በእርሱ ራስ ላይ አኑር” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 48:18
11 Cross References  

‘አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ንጹሕ ያል​ሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያ​ው​ቅም’ አልሁ።


ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ርኩስ፥ የሚ​ያ​ጸ​ይ​ፍም ከቶ በልች አላ​ው​ቅም” አለው።


ልባሞቹ ግን መልሰው ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ፤’ አሉአቸው።


እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤ እና​ንተ ወን​ዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈል​ጋ​ች​ኋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ” አላ​ቸው። ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ከፈ​ር​ዖን ፊት አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው።


“ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።


በፊ​ቱም በኵሩ እንደ ታላ​ቅ​ነቱ፥ ታና​ሹም እንደ ታና​ሽ​ነቱ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ደ​ነቅ ተያዩ።


ላባም እን​ዲህ አለ፥ “በሀ​ገ​ራ​ችን ታላ​ቂቱ ሳለች፥ ታና​ሺ​ቱን እን​ሰጥ ዘንድ ወግ አይ​ደ​ለም፤


ርብ​ቃም ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቤት የነ​በ​ረ​ውን የታ​ላ​ቁን ልጅ​ዋን የዔ​ሳ​ውን መል​ካ​ሙን ልብስ አመ​ጣች፤ ለታ​ናሹ ልጅዋ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አለ​በ​ሰ​ችው፤


ሎጥም አላ​ቸው፥ “ጌቶች ሆይ፥ በጀ በሉኝ፤


ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው።


አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements