Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 48:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጕልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዮሴፍም ከጉልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው፥ ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዮሴፍ ልጆቹን ከያዕቆብ ጒልበት ፈቀቅ አደረገና ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ ሰገደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዮሴፍም ከጕልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 48:12
15 Cross References  

ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት።


ልጆች ሆይ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ችሁ በጌ​ታ​ችን ታዘዙ፤ ይህ የሚ​ገባ ነውና።


ሴት​ዮ​ዋም ገብታ በእ​ግሩ አጠ​ገብ ወደ​ቀች በም​ድ​ርም ላይ ሰገ​ደች፤ ልጅ​ዋ​ንም አን​ሥታ ወጣች።


ቤር​ሳ​ቤ​ህም የአ​ዶ​ን​ያ​ስን ነገር ትነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ገባች፤ ንጉ​ሡም ሊቀ​በ​ላት ተነሣ፤ ሳማ​ትም፤ በዙ​ፋ​ኑም ተቀ​መጠ፤ ለን​ጉ​ሡም እናት ወን​በር አስ​መ​ጣ​ላት፤ በቀ​ኙም ተቀ​መ​ጠች።


“በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይፍራ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጎ​ነ​በ​ሰና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፦


“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።


እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።


አብ​ር​ሃ​ምም ተነሣ፤ በሀ​ገሩ ሕዝብ ፊትም ለኬጢ ልጆች ሰገደ።


ሁለ​ቱም መላ​እ​ክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰ​ዶም ከተማ በር ተቀ​ምጦ ነበር። ሎጥም ባያ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ተነሣ፤ ፊቱ​ንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገ​ደ​ላ​ቸው፤


ዐይ​ኑ​ንም በአ​ነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያ​ቸ​ውም ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተነ​ሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድ​ርም ሰገደ፤


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።


ዮሴ​ፍም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ወሰደ፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም በቀኙ በእ​ስ​ራ​ኤል ግራ፥ ምና​ሴ​ንም በግ​ራው በእ​ስ​ራ​ኤል ቀኝ አቆ​ማ​ቸው፤ ወደ አባ​ቱም አቀ​ረ​ባ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements