Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 43:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ብሩን በአ​ጠ​ፌታ አድ​ር​ጋ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ውሰዱ፤ በዓ​ይ​በ​ታ​ች​ሁም አፍ የተ​መ​ለ​ሰ​ውን ብር መል​ሳ​ችሁ ውሰዱ፤ ምና​ል​ባት ባለ​ማ​ወቅ ይሆ​ናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፣ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፥ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በፊት በየስልቻዎቻችሁ ጫፍ ተመልሶ የነበረው ገንዘብ በስሕተት ሊሆን ስለሚችል እጥፍ ገንዘብ ይዛችሁ ሂዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ብሩን በአጠፌታ አድርጋችሁ በእጃችሁ ውሰዱ በዓይበታችሁ አፍ የተመለሰውንም ብር መልሳችሁ ውሰዱ ምናልባት በስሕተት ይሆናል።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 43:12
12 Cross References  

ዮሴ​ፍም ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን እህል ይሞ​ሉት ዘንድ አዘዘ፤ የየ​ራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ብር በየ​ዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ይመ​ል​ሱት ዘንድ፥ ደግ​ሞም የመ​ን​ገድ ስንቅ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ አዘዘ። እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእ​ነ​ርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ብራ​ቸ​ውን በዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ተቋ​ጥሮ አገ​ኙት፤ እነ​ር​ሱም አባ​ታ​ቸ​ውም የተ​ቋ​ጠረ ብራ​ቸ​ውን አይ​ተው ፈሩ።


ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ትና​ን​ት​ናና ዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር እርሱ ነውና።


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብቻ ያይ​ደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መል​ካ​ሙን ነገር እና​ስ​ባ​ለ​ንና።


እርስ በር​ሳ​ችሁ ከመ​ዋ​ደድ በቀር ለማ​ንም ዕዳ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የወ​ደደ ግን ሕግን ሁሉ ፈጸመ።


ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ።


ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር ውሰዱ፤ ተነ​ሥ​ታ​ች​ሁም ወደ​ዚያ ሰው ውረዱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ ወደ​ም​ና​ድ​ር​በ​ትም ስፍራ በደ​ረ​ስን ጊዜ ዓይ​በ​ታ​ች​ንን ከፈ​ትን፤ እነ​ሆም፥ የየ​አ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ብር በየ​ዓ​ይ​በቱ አፍ ነበር፤ አሁ​ንም ብራ​ች​ንን በእ​ጃ​ችን እንደ ሚዛኑ መለ​ስ​ነው።


እህል እን​ሸ​ም​ት​በት ዘንድ ሌላም ብር በእ​ጃ​ችን አመ​ጣን፤ ብራ​ች​ን​ንም በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ማን እንደ ጨመ​ረው አና​ው​ቅም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements