Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 42:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፣ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቍጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዮሴፍ ወንድሞቹን ባያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቊጣ ቃል “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እህል ለመሸመት ከከነዓን አገር መጣን” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም ክፋ ቃልንም ተናገራቸው፦ እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 42:7
6 Cross References  

“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።”


በፊ​ቱም በኵሩ እንደ ታላ​ቅ​ነቱ፥ ታና​ሹም እንደ ታና​ሽ​ነቱ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ደ​ነቅ ተያዩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements