Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 42:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ያዕቆብም፣ “ልጄ ዐብሯችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፣ ሽበቴን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ያዕቆብም፥ “ልጄ አብሮአችሁ ወደዚያ አይወርድም፤ ወንድሙ እንደሆን ሞቷል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው። ይዛችሁት ስትሄዱ በመንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበት፥ ሽበቴን በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 እርሱም አለ፦ ልጅሴ ከእናንተ ጋር አይወርድም ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፋ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 42:38
20 Cross References  

ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድም ብን​ያ​ምን ግን ያዕ​ቆብ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር አል​ሰ​ደ​ደ​ውም፥ “ምና​ል​ባት ክፉ እን​ዳ​ያ​ገ​ኘው” ብሎ​አ​ልና።


እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ።


እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ችህ በከ​ነ​ዓን ምድር የም​ን​ኖር ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ ታና​ሹም እነሆ ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር ነው፤ ሌላ​ውም ሞቶ​አል።”


እስከ ሽም​ግ​ልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበ​ትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ሠር​ቻ​ለሁ፤ እኔም ይቅር እላ​ለሁ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ እን​ዲህ አልሁ፥ “በሕ​ይ​ወት ዘመኔ መካ​ከል ወደ ሲኦል በሮች እገ​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ዘመ​ኔን ተውሁ።


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።


ብቻ​ውን ተአ​ም​ራ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


አን​ተም እንደ ጥበ​ብህ አድ​ርግ፤ ሽበ​ቱ​ንም በሰ​ላም ወደ መቃ​ብር አታ​ው​ር​ደው።


እኛም ለጌ​ታዬ እን​ዲህ አልን፦ ሽማ​ግሌ አባት አለን፤ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደ​ውም ታናሽ ብላ​ቴና አለ፤ ወን​ድሙ ግን ሞተ፤ ለእ​ና​ቱም እርሱ ብቻ​ውን ቀረ፤ አባ​ቱም ይወ​ድ​ደ​ዋል።


ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ።


ሮቤ​ልም አባ​ቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላ​መ​ጣ​ሁት እን​ደ​ሆነ ሁለ​ቱን ልጆ​ችን ግደል፤ ልጅ​ህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።”


ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር ውሰዱ፤ ተነ​ሥ​ታ​ች​ሁም ወደ​ዚያ ሰው ውረዱ።


ጌታ​ዬ​ንም፦ ብላ​ቴ​ናው አባ​ቱን መተው አይ​ሆ​ን​ለ​ትም፤ የተ​ወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞ​ታ​ልና አል​ንህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements