Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 41:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድ​ሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴ​ፍም ከፈ​ር​ዖን ፊት ወጣ፤ የግ​ብፅ ምድ​ር​ንም ሁሉ ዞረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 41:46
15 Cross References  

ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመ​ል​ስ​ለት ዘንድ የም​ት​መ​ክ​ሩኝ ምን​ድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎ​ሞን በሕ​ይ​ወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ተማ​ከረ።


ዳዊ​ትም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመ​ትም ነገሠ፤


ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል መጣ፤ በፊ​ቱም ቆመ፤ እጅ​ግም ወደ​ደው፤ ለእ​ር​ሱም ጋሻ ጃግ​ሬው ሆነ።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር የአ​ባ​ቱን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ሚስ​ቶች ከባ​ላና ከዘ​ለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላ​ቴና ነበረ፤ ዮሴ​ፍም የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውን ወሬ ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ እስ​ራ​ኤል ያመጣ ነበር።


ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤


እን​ግ​ዲህ ከዚህ ከሚ​መ​ጣው ሁሉ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ማም​ለጥ እን​ድ​ት​ችሉ፥ በሰው ልጅ ፊትም እን​ድ​ት​ቆሙ ሁል​ጊዜ ትጉ።”


የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዕድ​ሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮ​ሴፍ ልጅም ይመ​ስ​ላ​ቸው ነበር።


ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።


እርሱ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ከእ​ርሱ ጋር ካደ​ጉ​ትና በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ብላ​ቴ​ኖች ጋር ተማ​ከረ።


በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ግብፅ ያስ​ገ​ኘ​ችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ።


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ዐወ​ቃ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ዮሴ​ፍም አይ​ቶት የነ​በ​ረ​ውን ሕልም ዐሰበ።


እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements