Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 41:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፣ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከዚያ በኋላ ሰባት የራብ ዓመቶች ይመጣሉ፤ ራብ አገሪቱን በብርቱ ስለሚጐዳት እነዚያ የጥጋብ ዓመቶች ይረሳሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ደግሞ ከዚህ በኍላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 41:30
15 Cross References  

በም​ድ​ርም ሁሉ እህል አል​ነ​በ​ረም፤ ራብ እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ ከራ​ብም የተ​ነሣ የግ​ብፅ ምድ​ርና የከ​ነ​ዓን ምድር ተጐዳ።


ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።


ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፤ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤


ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ።


እን​ዲ​ሁም በም​ድር ላይ የተ​ባ​ረኩ ይሆ​ናሉ፤ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፥ በም​ድ​ርም ላይ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው አም​ላክ ይም​ላ​ሉና፤ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንም ጭን​ቀት ረስ​ተ​ዋ​ልና፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ቡ​ት​ምና።


ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።


በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦ​ስት ዓመት ራብ በሀ​ገ​ርህ ላይ ይም​ጣ​ብ​ህን? ወይስ ጠላ​ቶ​ችህ እያ​ሳ​ደ​ዱህ ሦስት ወር ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሽን? ወይስ የሦ​ስት ቀን ቸነ​ፈር በሀ​ገ​ርህ ላይ ይሁን? የሚ​ሻ​ል​ህን ምረጥ። አሁ​ንም ለላ​ከኝ ምን መልስ እን​ደ​ም​ሰጥ አስ​ብና መር​ምር” ብሎ ነገ​ረው።


በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።


ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤”


ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።


በሆ​ዳ​ቸ​ውም ውስጥ የገባ እን​ደ​ሌለ ሆኑ፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ጀ​መ​ሪያ እንደ ነበ​ረው የከፋ ነበረ፤ ነቃ​ሁም። ዳግ​መ​ኛም ተኛሁ፤


በኋ​ላም ከሚ​ሆ​ነው ከዚያ ራብ የተ​ነሣ በም​ድር የሆ​ነው ጥጋብ አይ​ታ​ወ​ቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆ​ና​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements