Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ላሜ​ሕም ለሚ​ስ​ቶቹ ለዓ​ዳና ለሴላ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የላ​ሜሕ ሚስ​ቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጡ፤ እኔ ጐል​ማ​ሳ​ውን ስለ መቍ​ሰሌ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም ስለ መወ​ጋቴ ገድ​የ​ዋ​ለ​ሁና፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “ዓዳና ሴላ ሆይ ስሙኝ፤ የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤ አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣ ጕልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ላሜሕም ለሚስቶቹ፥ “ዓዳ እና ጺላ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ሆይ፥ የምለውን ስሙኝ፤ ቢያቆስለኝ ጐልማሳውን ገደልኩ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገደልኩ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ላሜክ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ እናንተ “ዓዳ እና ጺላ የላሜክ ሚስቶች ሆይ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ የምለውን ስሙ፤ አንድ ወጣት መትቶ ስላቈሰለኝ ገደልኩት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፤ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬን አድምጡ፤

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 4:23
7 Cross References  

በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ ስማ፤ የሶ​ፎር ልጅ ሆይ፥ ምስ​ክር ሁነህ አድ​ምጥ፤


አት​በ​ቀል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች ቂም አት​ያዝ፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።


“አት​ግ​ደል።


ይህ​ንም ነገር ለኢ​ዮ​አ​ታም በነ​ገ​ሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድም​ፁ​ንም አን​ሥቶ አለ​ቀሰ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “የሰ​ቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይስ​ማ​ችሁ።


ሴላም ደግሞ ቶቤ​ልን ወለ​ደች። እር​ሱም ናስና ብረ​ትን የሚ​ሠራ ሆነ። የእ​ኅ​ቱም ስም ኖሄም ነበረ።


በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።


ኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ለን፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንና ለመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንም እልል እን​በል፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements