Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 38:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነትኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኍትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 38:26
19 Cross References  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።


እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።


ሌሊቱ አል​ፎ​አል፤ ቀኑም ቀር​ቦ​አል። እን​ግ​ዲህ የጨ​ለ​ማን ሥራ ከእና እና​ርቅ፤ የብ​ር​ሃ​ን​ንም ጋሻ ጦር እን​ል​በስ።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤


ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?


አሁ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ይልቅ አብ​ዝ​ተሽ በሠ​ራ​ሽው ኀጢ​አ​ትሽ እኅ​ቶ​ች​ሽን ስላ​ረ​ከ​ስ​ሻ​ቸው ቅጣ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ። ከአ​ን​ቺም ይልቅ አጸ​ደ​ቅ​ሻ​ቸው፤ አን​ችም እፈሪ፤ እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ተሸ​ከሚ፤ እኅ​ቶ​ች​ሽን አጽ​ድ​ቀ​ሻ​ቸ​ዋ​ልና።


አንድ ጊዜ ተና​ገ​ርሁ፥ ሁለ​ተኛ ጊዜም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ና​ገ​ርም።”


አሁን ግን ሕማም በአ​ንተ ላይ መጥቶ ዳሰ​ሰህ። አን​ተም ተቸ​ገ​ርህ።


ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን የሚ​መ​ታ​ውን መል​አክ ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድ​ያ​ለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አደ​ረጉ? እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።


ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።


ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም በሰ​ገ​ነት ላይ ድን​ኳን ተከ​ሉ​ለት፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባ​ቶች ገባ።


እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና።


እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ።


አዳ​ምም ሚስ​ቱን ሔዋ​ንን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ቃየ​ል​ንም ወለ​ደ​ችው።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ፋንታ በጎ መል​ሰ​ህ​ል​ኛ​ልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements