Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 38:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ይሁ​ዳም በአ​ያት ጊዜ ዘማ መሰ​ለ​ችው፤ ፊቷን ተሸ​ፍና ነበ​ርና አላ​ወ​ቃ​ትም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት ዐዳሪ መሰለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፥ ይሁዳ ዝሙት ዐዳሪ መሰለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ፊቷን በሻሽ ሸፍና ስለ ነበር ይሁዳ ባያት ጊዜ አመንዝራ ሴት መሰለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ይሁዳም ባያት ጊዜ ጋለሞታን መሰለችው ፊትዋን ተሸፍና ነበርና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 38:15
4 Cross References  

እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና።


ወደ እር​ስ​ዋም አዘ​ነ​በለ፥ “እባ​ክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እር​ስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላ​ወ​ቀም ነበ​ርና። እር​ስ​ዋም፥ “ወደ እኔ ብት​ገባ ምን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ?” አለ​ችው።


የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።


ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements