Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 36:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ቴም​ና​ሕም ለዔ​ሳው ልጅ ለኤ​ል​ፋዝ ዕቅ​ብት ነበ​ረች፤ አማ​ሌ​ቅ​ንም ለኤ​ል​ፋዝ ወለ​ደ​ች​ለት፤ የዔ​ሳ​ውም ሚስት የሐ​ዳሶ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ቲምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ቁባት ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የዔሳው ልጅ ኤሊፋዝ ቲመናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርስዋ ለኤሊፋዝ ዐማሌቅን ወለደችለት፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ የጭን ገረስ ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 36:12
10 Cross References  

“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


የሉ​ጣን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሖሪ፥ ሃማን ናቸው፤ የሉ​ጣ​ንም እኅት ትም​ናዕ ናት።


ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ሳፍር፥ ጎታም፥ ቄኔዝ፥ ቴም​ናስ፥ አማ​ሌቅ።


የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ።


የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሲም፥ ሞዛህ፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements