Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 32:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ሊቀበልህ በመምጣት ላይ ነው፤ አራት መቶ ሰዎችም ዐብረውት አሉ” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 32:6
14 Cross References  

ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤


ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።


አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና።


ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አለ፥ “ዔሳው መጥቶ አን​ዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀ​ረው ወገን ይድ​ናል።”


ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ፈራ፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አጣ። ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ​ትን ሰዎች ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም ሁለት ወገን አድ​ርጎ ከፈ​ላ​ቸው፤


መን​ጎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ የቤ​ቱ​ንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ያገ​ኛ​ቸ​ውን ከብ​ቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ከነ​ዓን ምድር ሄደ።


ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ።


ዔሳ​ውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተ​ው​ል​ህን?” አለ። እር​ሱም፥ “ይህ ለም​ን​ድን ነው? በጌ​ታዬ ዘንድ ሞገ​ስን ማግ​ኘቴ ይበ​ቃ​ኛል” አለ።


ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንተ አዳ​ን​ኸን፤ በጌ​ታ​ች​ንም ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘን፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሆ​ና​ለን” አሉት።


ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።


እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ከባሪያዎችህ እንደ አንዲቱ ሳልሆን አጽናንተኽኛልና፥ የባሪያህንም ልብ ደስ አሰኝተሃልና በዓይንህ ሞገስ ላግኝ አለችው።


እር​ስ​ዋም፥ “ባር​ያህ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገ​ኘች” አለ​ችው። ሴቲ​ቱም መን​ገ​ድ​ዋን ሄደች፤ ወደ ቤት​ዋም ገባች፤ ከባ​ሏም ጋር በላች፤ ጠጣ​ችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘ​ን​ተኛ መስሎ አል​ታ​የም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements