Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 32:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወ​ር​ችን ሹልዳ አይ​በ​ሉም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ጭን ይዞ የወ​ር​ቹን ሹልዳ አደ​ን​ዝ​ዞ​አ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ ሹልዳን ከጭኑ ጋራ የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም በጭኑ መጋጠሚያ ላይ ያለው የያዕቆብ ሹልዳ ተነክቶ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ስለዚህም የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ ነክቶታልና፥ የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን (በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን) ሹልዳ አይበሉም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርችን ሹልዳ አደንዝዞአልን።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 32:32
6 Cross References  

ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።


እን​ዳ​ላ​ሸ​ነ​ፈ​ውም ባየ ጊዜ የጭ​ኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጭኑ ሹልዳ ሲታ​ገ​ለው ደነ​ዘዘ።


ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር።


ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤


ከዚ​ያም ወደ ፋኑ​ሄል ወጣ፤ ለፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች እን​ዲሁ አላ​ቸው፤ የፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች የሱ​ኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለ​ሱ​ለት።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሰቂ​ማን ሠርቶ በዚያ ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከዚያ ወጥቶ ፋኑ​ኤ​ልን ሠራ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements