Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 32:11
21 Cross References  

ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው። በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።


እጆ​ቼን ወደ አንተ ዘረ​ጋሁ፤ ነፍ​ሴም እንደ ምድረ በዳ አን​ተን ተጠ​ማች።


አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት በል​ቡም ሽን​ገላ የሌ​ለ​በት ሰው ብፁዕ ነው።


አቤቱ፥ ጽድ​ቄን ስማኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ም​ጠኝ፤ በተ​ን​ኰ​ለ​ኛም ከን​ፈር ያል​ሆ​ነ​ውን ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፤


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ?


እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተን በዓ​ሊ​ም​ንና ምስ​ሎ​ቹን በማ​ም​ለ​ካ​ችን በድ​ለ​ናል፤ አሁ​ንም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ አድ​ነን፤ እና​መ​ል​ክ​ሃ​ለ​ንም” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ ።


ዔሳ​ውም አባቱ ስለ ባረ​ከው በያ​ዕ​ቆብ ቂም ያዘ​በት፤ ዔሳ​ውም በልቡ አለ፥ “ለአ​ባቴ የል​ቅሶ ቀን ትቅ​ረብ፤ ወን​ድ​ሜን ያዕ​ቆ​ብን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ።”


“በመ​ን​ገድ በማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ ላይ ወይም በመ​ሬት ላይ ከጫ​ጭ​ቶ​ችና ከእ​ን​ቍ​ላል ጋር እና​ቲቱ በእ​ነ​ዚህ ላይ ተቀ​ምጣ የወፍ ጎጆ ብታ​ገኝ እና​ቲ​ቱን ከጫ​ጭ​ቶ​ችዋ ጋር አት​ው​ሰድ።


ለር​ብ​ቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነ​ገ​ራት፤ ታና​ሹን ልጅ​ዋን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ልካ ጠራ​ችው፤ አለ​ች​ውም፥ “እነሆ ወን​ድ​ምህ ዔሳው ያድ​ድ​ን​ሃል፤ ሊገ​ድ​ል​ህም ይፈ​ል​ጋል።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ፈራ፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አጣ። ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ​ትን ሰዎች ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም ሁለት ወገን አድ​ርጎ ከፈ​ላ​ቸው፤


ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”


ንጉሡ ዳዊ​ትም ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements