Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 31:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 አንተ ወደ አባትህ ቤት ለመመለስ ስለ ናፈቅህ ሄደሃል፤ ነገር ግን የቤቴን የጣዖት ምስል የሰረቅኸው ለምንድን ነው?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 አሁንም የአባትህን ቤት እጅጉን ናፍቆሃልና ሂድ፥ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደ ተለየኸኝ ዐውቃለሁ፤ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅህብኝ ለምንድን ነው?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 አሁንም የአባትህን ቤት ከናፈቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 31:30
17 Cross References  

እር​ሱም፥ “የሠ​ራ​ኋ​ቸ​ውን አማ​ል​ክ​ቴን፥ ካህ​ኑ​ንም ይዛ​ችሁ ሄዳ​ች​ኋል፤ ለእኔ ምን ተዋ​ች​ሁ​ልኝ? እና​ን​ተስ፦ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ እን​ዴት ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ?” አለ።


ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች።


እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ቤቶች እሳ​ትን ያነ​ድ​ዳል፤ ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ው​ማል፤ ይማ​ር​ካ​ቸ​ው​ማል፤ እረ​ኛም ልብ​ሱን እን​ደ​ሚ​ቀ​ምል እን​ዲሁ የግ​ብ​ፅን ሀገር ይቀ​ም​ላ​ታል፤ ከዚ​ያም በሰ​ላም ይወ​ጣል።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወሰ​ዱ​አ​ቸው።


ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው።


በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው።


እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ልጆ​ች​ህ​ንና ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ከእኔ የም​ት​ቀ​ማኝ ስለ​መ​ሰ​ለ​ኝና ስለ​ፈ​ራሁ ይህን አደ​ረ​ግሁ።”


ያዕ​ቆ​ብም ለቤተ ሰቡና ከእ​ርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር ያሉ እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም እጠቡ፤


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የና​ኮር አባት ታራ፥ አስ​ቀ​ድ​መው በወ​ንዝ ማዶ ተቀ​መጡ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ።


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሊሰ​ልሉ ሄደው የነ​በ​ሩት አም​ስቱ ሰዎች መጥ​ተው ወደ​ዚያ ገቡ፤ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም የጦር ዕቃ ከታ​ጠ​ቁት ከስ​ድ​ስት መቶ ሰዎች ጋር በደ​ጃፉ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ምዋ​ር​ቱን ያም​ዋ​ርት ዘንድ፥ በት​ሩን ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖ​ቱ​ንም ይጠ​ይቅ ዘንድ በሁ​ለት መን​ገ​ዶች ራስ ላይ ይቆ​ማል።


እር​ሱም፥ “አል​ሄ​ድም፥ ነገር ግን ወደ ሀገ​ሬና ወደ ዘመ​ዶች እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements