Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እን​ዲ​ህም ሆነ፦ በጎቹ በሚ​ፀ​ን​ሱ​በት ወራት በበ​ት​ሮቹ አም​ሳል ይፀ​ንሱ ዘንድ ያዕ​ቆብ በት​ሮ​ቹን በበ​ጎቹ ፊት በውኃ ማጠጫ ገን​ዳው ውስጥ ያኖ​ራ​ቸው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ፣ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎቹ ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እንዲህም ሆነ፥ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:41
3 Cross References  

በጎ​ቹም ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በት​ሮቹ በፊ​ታ​ቸው ይሆኑ ዘንድ የላ​ጣ​ቸ​ውን በት​ሮች በውኃ ማጠጫ ገን​ዳው ውስጥ አኖ​ራ​ቸው፤


ያዕ​ቆ​ብም ተባት በጎ​ች​ንና እን​ስት በጎ​ችን ለይቶ ነጭና ሐመደ ክቦ በሆኑ አው​ራ​ዎች ፊት አቆ​ማ​ቸው፤ መን​ጎ​ቹ​ንም ለብ​ቻ​ቸው አቆ​ማ​ቸው። ከላባ በጎች ጋርም አል​ጨ​መ​ራ​ቸ​ውም።


በጎ​ችም ከወ​ለዱ በኋላ በፊ​ታ​ቸው በት​ሩን አያ​ደ​ር​ገ​ውም ነበር፤ ምል​ክት ያላ​ቸው ለያ​ዕ​ቆብ፥ ምል​ክት የሌ​ላ​ቸ​ውም ለላባ ሆኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements