Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አሁን ግን ፈጽ​መው በዝ​ተ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኔ መም​ጣት ባር​ኮ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን ደግሞ ለቤቴ የም​ሠ​ራው መቼ ነው?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበረው ሀብትህ ዛሬ ተትረፍርፏል፣ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ስለ ራሴ ቤት የማስበው መቼ ነው?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፤ ወደ አንተ በመምጣቴ እግዚአብሔር ባረክህ፤ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:30
7 Cross References  

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።


እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤


ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር፥ በአ​ት​ክ​ልት ስፍራ እን​ደ​ሚ​ዘሩ ዘር​ህን እንደ ዘራ​ህ​ባት፥ በእ​ግ​ር​ህም እን​ዳ​ጠ​ጣ​ሃት፥ እንደ ወጣ​ህ​ባት እንደ ግብፅ ምድር አይ​ደ​ለ​ችም።


ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “እን​ዴት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ል​ሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብ​ቶ​ችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ጥቂት ሆነው አግ​ኝ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤


ላባም፥ “የም​ሰ​ጥህ ምን​ድን ነው?” አለው። ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “ምንም አት​ስ​ጠኝ፤ ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ር​ግ​ልኝ እን​ደ​ገና በጎ​ች​ህን አሰ​ማ​ራ​ለሁ፤ እጠ​ብ​ቃ​ለ​ሁም።


ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ባለ​ጠጋ ሆነ፤ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ብዙ ከብ​ትም፤ ላሞ​ችም፥ በጎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችና አህ​ዮ​ችም ሆኑ​ለት።


ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements