Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እር​ስ​ዋም፥ “ባሪ​ያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እር​ስዋ ግባ፤ በእ​ኔም ጭን ላይ ትው​ለድ፤ የእ​ር​ስ​ዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁ​ኑ​ልኝ” አለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሷም፣ “እነሆ፤ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከርሷ ጋራ ተኛ” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሷም ባርያዬ ባላ እነሆ አለች፥ ድረስባት፥ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርሷም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርስዋም “እነሆ፥ አገልጋዬ ባላ እዚህ አለች፤ በእኔ ምትክ ልጅ እንድትወልድልኝ ወደ እርስዋ ግባ፤ በዚህ ዐይነት በእርስዋ አማካይነት የልጆች እናት እሆናለሁ” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እርስዋምም ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ድረስባት፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:3
6 Cross References  

ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።


ጕል​በ​ቶች ስለ ምን ደገ​ፉኝ? ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።


ልያም መው​ለ​ድን እን​ዳ​ቆ​መች በአ​የች ጊዜ አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን ዘለ​ፋን ወሰ​ደች፤ ሚስት ትሆ​ነ​ውም ዘንድ ለያ​ዕ​ቆብ ሰጠ​ችው፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ።


ላባ ለልጁ ለራ​ሔል የሰ​ጣት የባላ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ባላ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements