Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 30:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ያዕ​ቆ​ብም አለው፥ “እን​ዴት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ል​ሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብ​ቶ​ችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ጥቂት ሆነው አግ​ኝ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ያዕቆብም እንዲህ አለው፤ “መቼም እንዴት እንዳገለገልሁህ፣ ከብቶችህ በእኔ ጥበቃ ምን ያህል እንደ ተመቻቸው አንተ ታውቃለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እርሱም አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ያዕቆብም እንዲህ አለው “እንዴት እንዳገለገልኩህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደ ረባልህ አንተ ታውቃለህ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እርሱም አለው፦ እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 30:29
10 Cross References  

እኔ ባለኝ ጕል​በቴ ሁሉ አባ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ሎሌዎች ሆይ! ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።


በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤


“እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?


የራ​ሔል አገ​ል​ጋይ ባላም ፀነ​ስች፤ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት።


አሁን ግን ፈጽ​መው በዝ​ተ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኔ መም​ጣት ባር​ኮ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን ደግሞ ለቤቴ የም​ሠ​ራው መቼ ነው?”


Follow us:

Advertisements


Advertisements