ዘፍጥረት 27:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 እርሱም ደግሞ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አመጣ፤ አባቱንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ልጅህ ከአደነው ብላ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ በማዘጋጀት ለአባቱ አቅርቦ፣ “አባቴ ሆይ፤ እንድትመርቀኝ፣ እስኪ ቀና በልና ካደንሁት ብላ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አገባ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ይነሣ፥ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና “አባቴ ሆይ፥ እንድትመርቀኝ፥ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ ለአባቱም አገባ አባቱንም፦ አባቴ ይነሣ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ አለው። See the chapter |