ዘፍጥረት 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንዲህም ሆነ፦ ይስሐቅ ፈጽሞ ከአረጀ በኋላ ዐይኖቹ ፈዝዘው አያይም ነበር። ታላቁን ልጁን ዔሳውንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ይሥሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ፈዘው ነበር፤ ታላቁን ልጁን ዔሳውን “ልጄ ሆይ!” ብሎ ጠራው፤ ልጁም “እነሆ፥ አለሁ!” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው። See the chapter |