Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን ጠራ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ሚስ​ትህ ናት፤ እን​ዴ​ትስ እር​ስ​ዋን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስ​ሐ​ቅም፥ “በእ​ር​ስዋ ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሞት ብዬ ነው” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አቢሜሌክም ይሥሐቅን ጠርቶ፣ “እርሷ ሚስትህ ሆና ሳለች፣ እንዴት ‘እኅቴ ናት’ ትላለህ?” አለው። ይሥሐቅም፣ “በርሷ ሰበብ፣ ሕይወቴን እንዳላጣ ብዬ ነው” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ “እነሆ ሚስትህ ናት፥ እንዴትስ እርሷን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስሐቅም፦ “በእርሷ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህ አቤሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ “ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ ‘እኅቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኛል ብዬ ስለ ፈራሁ ነው” ብሎ መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ እነሆ ሚስትህ ናት እንዴትስ እርስዋን፦ እኅቴ ናትአልህ? ይስሐቅም፦ በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው አለው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 26:9
5 Cross References  

በዚ​ያም ብዙ ቀን ተቀ​መጠ። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በመ​ስ​ኮት ሆኖ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ ይስ​ሐ​ቅን ከሚ​ስቱ ከር​ብቃ ጋር ሲጫ​ወት አየው።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።”


ፈር​ዖ​ንም አብ​ራ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ ምን​ድን ነው? እር​ስዋ ሚስ​ትህ እንደ ሆነች ለምን አል​ገ​ለ​ጥ​ህ​ል​ኝም?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ፊል​ጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብ​ሬ​አ​ችሁ ስኖር አታ​ወ​ቀ​ኝ​ምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አብን አሳ​የን ትላ​ለህ?


ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements