Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 26:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር እንደ አለ በአ​የን ጊዜ በአ​ን​ተና በእኛ መካ​ከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፤ እኛም በአ​ንተ ላይ ክፉ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ እን​ማ​ማ​ላ​ለን።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 አንተን እንዳልጐዳንህ፣ ነገር ግን በጎነትን እንዳሳየንህና በሰላም እንደ ሸኘንህ ሁሉ፣ አንተም ክፉ እንዳታደርግብን በመካከላችን ውል ይደረግ፤ አንተን እንደሆን መቼም እግዚአብሔር ባርኮሃል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እኛ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በሰላምም እንደ ሰደድንህ፥ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን፥ አንተ አሁንም ከጌታ ዘንድ የተባረክህ ነህ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ እንዳልሠራን አንተም በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ዘወትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግንብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ስለዚህም፦ በእኛን በአንተ መካከል መሐላ ይሁን እኝ አንተን እንዳልነካንህ፥ በጎነትንም ብቻ እንዳሳየንህ፥ በደኅናም እንደ ሰደድንህ አንተም ክፉ እንዳትሠራብን ቃል ኪዳን ከአንተ ጋር እናድርግ አልን አንተ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረክህ ነህ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 26:29
8 Cross References  

እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”


በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements