Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 26:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ይሥሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚያም መሠዊያን ሠራ የጌታንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ፥ የይስሐቅም አገልጋዮች በዚያ ጉድጓድ ማሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚይም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 26:25
11 Cross References  

አብ​ራ​ምም ድን​ኳ​ኑን ነቀለ፤ መጥ​ቶም በኬ​ብ​ሮን ባለው የመ​ምሬ ዛፍ ተቀ​መጠ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ።


ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚ​ያም ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ምህ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸህ ጊዜ ለተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ለእኔ መሥ​ው​ያን ሥራ።”


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው።


ስፍ​ራ​ውም አስ​ቀ​ድሞ መሠ​ውያ የሠ​ራ​በት ነው፤ በዚ​ያም አብ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ።


ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ።


ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙ​ንም ሄኖስ አለው፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት የጀ​መረ ነው።


በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements