Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 ርብ​ቃም ተነ​ሣች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም፥ በግ​መ​ሎ​ችዋ ላይ ተቀ​ም​ጠው ከሰ​ው​ዬው ጋር አብ​ረው ሄዱ፤ ሎሌ​ውም ርብ​ቃን ተቀ​ብሎ ሄደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ከዚያም ርብቃና አገልጋዮቿ ተዘጋጁ፤ ግመሎቻቸውም ላይ ወጥተው ሰውየውን ተከተሉት፤ በዚህ ሁኔታ አገልጋዩ ርብቃን ይዟት ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 ርብቃም ተነሣች ደንገጥሮችዋም፥ በግመሎችም ላይ ተቀምጠው ያንን ሰው ተከተሉት፥ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 ከዚህ በኋላ ርብቃ ከደንገጡሮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 ርብቃም ተነሣች ደንገጥሮችዋም በግመሎችም ላይ ተቀምጠው ያንን ሰው ተከተሉት፤ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:61
10 Cross References  

ልብ አድ​ርጉ፥ እኔም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ፥ በም​ድ​ርም ላይ ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።


ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም።


እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።


ይስ​ሐ​ቅም በዐ​ዘ​ቅተ ራእይ በኩል ወደ ምድረ በዳ ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በአ​ዜብ በኩል ባለው ምድር ተቀ​ምጦ ነበ​ርና።


ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ።


አቤ​ግ​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ በአ​ህ​ያም ላይ ተቀ​መ​ጠች፤ አም​ስ​ቱም ገረ​ዶ​ችዋ ተከ​ተ​ሉ​አት፤ የዳ​ዊ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተከ​ትላ ሄደች፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements