Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 እርሱ ግን፣ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እንድመለስ አሰናብቱኝ” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 እርሱም፦ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፥ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 እርሱ ግን “እባካችሁ አታቈዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብዬ ወደ ጌታዬ ልመለስ” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 እርሱም፦ እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:56
8 Cross References  

እኔ ራሴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ፤ አም​ጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱም ትከ​ና​ወ​ን​ለ​ታ​ለች።


የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።


እር​ሱም አለኝ፦ አካ​ሄ​ዴን በፊቱ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከአ​ንተ ጋር ይል​ካል። መን​ገ​ድ​ህ​ንም ያቀ​ናል፤ ለል​ጄም ከወ​ገ​ኖች ከአ​ባ​ቴም ቤት ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን እን​ጥ​ራና ከአ​ፍዋ እን​ጠ​ይቅ” አሉ።


ራሔ​ልም ዮሴ​ፍን ከወ​ለ​ደች በኋላ ያዕ​ቆብ ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ስፍ​ራዬ፥ ወደ ሀገ​ሬም እመ​ለስ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements