Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 የአብርሃም አገልጋይ ያሉትን በሰማ ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:52
12 Cross References  

ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ።


ሰው​የ​ውም ደስ አለው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገደ።


እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥ ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በም​ድር ላይ ሰገደ፤ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደቁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገዱ።


ዳዊ​ትም ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” አላ​ቸው። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፥ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ተን​በ​ር​ክ​ከው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ፤ ደግ​ሞም ለን​ጉሡ።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


ርብቃ እን​ኋት፤ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃት ሂድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ለጌ​ታህ ልጅ ሚስት ትሁን።”


እኔም ደግሞ ዕድ​ሜ​ውን ሙሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements