Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 እኔም በልቤ ያሰ​ብ​ሁ​ትን ሳል​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እን​ስ​ራ​ዋን በት​ከ​ሻዋ ተሸ​ክማ ወጣች፥ ወደ ምን​ጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠ​ጪኝ” አል​ኋት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 “በልቤ የምጸልየውን ጸሎት ገና ሳልጨርስ፣ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች፤ ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ ቀዳች። እኔም፣ ‘እባክሽ፤ ውሃ አጠጪኝ’ አልኋት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 “እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም፥ እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ ‘እስኪ አጠጪኝ’ አልኋት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 የኅሊና ጸሎቴን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጒድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም ‘እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ’ አልኳት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ እስኪ አጠጭኝ አልኍት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:45
14 Cross References  

ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የዛሬ አራት ቀን በዘ​ጠኝ ሰዓት በዚች ሰዓት በቤቴ ስጸ​ልይ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብስ የለ​በሰ አንድ ሰው በፊቴ ቆሞ ታየኝ።


“ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም ከድ​ካ​ማ​ችን ይረ​ዳ​ናል፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ተስ​ፋ​ች​ንን ካላ​ወ​ቅን ጸሎ​ታ​ችን ምን​ድ​ነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ መከ​ራ​ች​ንና ስለ ችግ​ራ​ችን ይፈ​ር​ድ​ል​ናል።


ያን ጊዜ ትጠ​ራ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ማ​ሃል፤ ትጮ​ኻ​ለህ፤ እር​ሱም፦ እነ​ሆኝ፥ ይል​ሃል። የዐ​መፅ እስ​ራ​ትን ከመ​ካ​ከ​ልህ ብታ​ርቅ፥ ጣት​ህ​ንም መጥ​ቀስ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ር​ንም ብት​ተው፥


ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሰ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ የባ​ሪ​ያ​ህን ጆሮ ከፈ​ትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ አልህ፤ ስለ​ዚ​ህም ባሪ​ያህ ይህ​ችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።


እር​ስ​ዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግ​ሞም ለግ​መ​ሎ​ችህ እቀ​ዳ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ ልጅ ለባ​ሪ​ያዉ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጃት ሚስት እር​ስዋ ትሁን። በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements