Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ዛሬም ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ መጣሁ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ዛሬ የም​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ዴን ብታ​ቀ​ና​ልኝ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 “እኔም ዛሬ ወደ ውሃው ጕድጓድ ስደርስ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቃድህ ቢሆን የመጣሁበትን ጕዳይ አቃናልኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 “ከዚህም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጒድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ እንዲህም አልሁ፦ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፤

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:42
14 Cross References  

ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።


ወደ እና​ንተ እመጣ ዘን​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃዱ መን​ገ​ዴን ያቃ​ና​ልኝ ዘንድ ዘወ​ትር እጸ​ል​ያ​ለሁ።


ከስ​ን​ፍ​ና​ዬም ፊት የተ​ነሣ አጥ​ን​ቶቼ ሸተቱ፥ በሰ​በ​ሱም፤


በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ወገ​ኖች ሁሉ የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ለት ነው፤ ቅዱስ መል​አክ ተገ​ልጦ አን​ተን ወደ ቤቱ እን​ዲ​ጠ​ራህ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ው​ንም እን​ዲ​ሰማ አዝ​ዞ​ታል፤” አሉት።


ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ።


እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”


ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”


ሐናም በል​ብዋ ትና​ገር ነበር፤ ድም​ፅ​ዋም ሳይ​ሰማ ከን​ፈ​ር​ዋን ታን​ቀ​ሳ​ቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከ​ረች ቈጠ​ራት።


ብላ​ቴ​ና​ውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በዚ​ህች ከተማ አለ፤ እር​ሱም የተ​ከ​በረ ሰው ነው፤ የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጸ​ማል፤ አሁ​ንም ወደ​ዚያ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገድ ይነ​ግ​ረ​ና​ልና” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements