Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ጉት​ቻ​ው​ንና አም​ባ​ሮ​ቹን በእ​ኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእ​ኅ​ቱ​ንም የር​ብ​ቃን ነገር፦ ያ ሰው እን​ዲህ አለኝ ያለ​ች​ውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደ​ዚያ ሰው መጣ፤ እነ​ሆም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ከግ​መ​ሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እኅቱ ያደረገችውን የወርቅ ቀለበትና አምባሮች እንዳየ፣ እንዲሁም ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር እንደ ሰማ፣ ወዲያውኑ ወደ ሰውየው ሄደ፤ በምንጩም ዳር ከግመሎቹ አጠገብ ቆሞ አገኘው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ቀለበቱንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ “ያ ሰው እንዲህ አለኝ” ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፥ እነሆም፥ በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጒትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ያላትን ስትናገር ስለ ሰማም ነው። እርሱንም በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ቀለበቱንን አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ የእኅቱን የርብቃንም ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ እነሆም በውኃው ምንጭ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:30
7 Cross References  

ግመ​ሎ​ቹም ከጠጡ በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው​ዬው አንድ አንድ ወቄት የሚ​መ​ዝን የወ​ርቅ ጉትቻ፥ ለእ​ጆ​ች​ዋም ዐሥር ወቄት የሚ​መ​ዝን ጥንድ የወ​ርቅ አም​ባር አወጣ፤


ለር​ብ​ቃም ስሙ ላባ የተ​ባለ ወን​ድም ነበ​ራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ ወደ ሰው​ዬው ሮጠ።


እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”


የበ​ገ​ና​ውን አው​ታር ድምፅ ይቃ​ኛሉ፤ ከብዙ ሰዎ​ችም ጉባኤ ጋር ሰካ​ራ​ሞቹ ከም​ድረ በዳ መጡ፤ በእ​ጃ​ቸው አን​ባር፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ዋበ አክ​ሊል አደ​ረጉ።


እና​ቱ​ንም፥ “ከአ​ንቺ ዘንድ የተ​ሰ​ረ​ቀው፥ የረ​ገ​ም​ሽ​በ​ትም፥ በጆ​ሮ​ዬም የተ​ና​ገ​ር​ሽ​በት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስ​ጄው ነበር” አላት። እና​ቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ” አለ​ችው።


የጆሮ እን​ጥ​ል​ጥ​ሉ​ንም፥ አን​ባ​ሩ​ንም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ው​ንም፥ ቀጸ​ላ​ው​ንም፥


በውኑ ሙሽራ ጌጥ​ዋን ወይስ ድን​ግል ዝር​ግፍ ጌጥ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ሕዝቤ ግን ለማ​ይ​ቈ​ጠር ወራት ረስ​ቶ​ኛል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements