Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ለር​ብ​ቃም ስሙ ላባ የተ​ባለ ወን​ድም ነበ​ራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ ወደ ሰው​ዬው ሮጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱም ሰውየው ወዳለበት የውሃ ጕድጓድ ፈጥኖ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ለርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፥ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ምንጭ ወደ ሰውዬው ሮጠ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጒድጓድ እየሮጠ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ለርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ምንጭ ወደ ሰውዮው ሮጠ

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:29
8 Cross References  

እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከካ​ራን ነን” አሉት። “የና​ኮ​ርን ልጅ ላባን ታው​ቁ​ታ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እና​ው​ቀ​ዋ​ለን” አሉት።


ላባም የእ​ኅ​ቱን የር​ብ​ቃን ልጅ የያ​ዕ​ቆ​ብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀ​በ​ለው ሮጠ፥ አቅ​ፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገ​ባው። ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ለላባ ነገ​ረው።


አባቷ እና​ቷና ወን​ድ​ምዋ፦ “ብላ​ቴ​ና​ዪቱ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ በእኛ ዘንድ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ለች” አሉ።


እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።


ጉት​ቻ​ው​ንና አም​ባ​ሮ​ቹን በእ​ኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእ​ኅ​ቱ​ንም የር​ብ​ቃን ነገር፦ ያ ሰው እን​ዲህ አለኝ ያለ​ች​ውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደ​ዚያ ሰው መጣ፤ እነ​ሆም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ከግ​መ​ሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።


ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፤ ተነ​ሣና በሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል ወደ ካራን ምድር ወደ ወን​ድሜ ወደ ላባ ሂድ፤


ተነ​ሣና ወደ እና​ትህ አባት ወደ ባቱ​ኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሂድ፤ ከዚ​ያም ከእ​ና​ትህ ከር​ብቃ ወን​ድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አግባ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements