Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ” አለ​ችው፤ ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከጫ​ን​ቃዋ በእ​ጅዋ አው​ርዳ እስ​ኪ​ረካ አጠ​ጣ​ችው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሷም፣ “ጌታዬ፤ ጠጣ” አለችው፤ ፈጥናም እንስራዋን ወደ እጇ አውርዳ አጠጣችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሷም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ” አለችው፥ ፈጥናም እንስራዋን በእጇ አውርዳ አጠጣችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርስዋም “እሺ ጌታዬ ጠጣ” አለችና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ ዘንበል አድርጋ ያዘችለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርስዋም፦ ጌታዬ ሆይ ጠጣ አለችው ፈጥና፥ እንስራዋን በእጅዋ አውርዳ አጠጣችው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 24:18
6 Cross References  

በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤


እን​ስ​ራ​ሽን አዘ​ን​ብ​ለሽ ውኃ አጠ​ጭኝ የም​ላት እር​ስ​ዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ እስ​ኪ​ረኩ አጠ​ጣ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እር​ስዋ ለባ​ሪ​ያህ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጀ​ሃት ትሁን፤ በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”


ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከት​ከ​ሻዋ አወ​ረ​ደ​ችና፥ “አንተ ጠጣ፤ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ አጠ​ጣ​ለሁ” አለ​ችኝ፤ እኔም ጠጣሁ፤ ግመ​ሎ​ች​ንም ደግሞ አጠ​ጣች።


ውኃም ልታ​መ​ጣ​ለት በሄ​ደች ጊዜ ወደ እር​ስዋ ጠርቶ፥ “እግረ መን​ገ​ድ​ሽን ቍራሽ እን​ጀራ በእ​ጅሽ አም​ጭ​ልኝ” አላት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements