Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእግዚአብሔርም መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የጌታ መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የእግዚአብሔር መልአክ ሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራውና እንዲህ አለው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለትኛ ጊዜ ጠራው፦ እንዲህም አለው፦

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 22:15
15 Cross References  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እስ​ከ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ድረስ ዘር​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፥” አላት።


አብ​ር​ሃ​ምም ዛሬ በዚህ ተራራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ታየኝ ሲል ያን ቦታ “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ለም​ት​ወ​ድ​ደው ልጅ​ህም ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ምና መባ​ረ​ክን እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሙሴ በእ​ሳት ነበ​ል​ባል በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል ታየው፤ እነ​ሆም፥ ቍጥ​ቋ​ጦው በእ​ሳት ሲነ​ድድ፥ ቍጥ​ቋ​ጦ​ውም ሳይ​ቃ​ጠል አየ።


ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ።


ቃሌ ከአፌ በጽ​ድቅ ወጥ​ታ​ለች፤ አት​መ​ለ​ስ​ምም፤ ጕል​በት ሁሉ ለእኔ ይን​በ​ረ​ከ​ካል፤ ምላ​ስም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ላል ብዬ በራሴ ምያ​ለሁ።”


የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያሱ እንዲህ ሲል አዳኘበት፦


በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።


“አርባ ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በበ​ረሃ በደ​ብረ ሲና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ታየው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ዉን በሰ​ጠው ጊዜ ይም​ል​በት ዘንድ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ባይ​ኖር፥ በራሱ ማለ።


በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements