Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 21:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ስለዚህ ቦታው፣ ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ ቤርሳቤህ ተባለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፥ ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፤ ከዚያ ሁለቱ ተማምልዋልና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 21:31
14 Cross References  

ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።


አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።


በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።


እኔ እን​ዲህ እመ​ክ​ር​ሃ​ለሁ፤ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ አን​ተም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


ኮላ​ሴ​ዎል፥ ቤር​ሳ​ቤ​ሕና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ከዚ​ያም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ ሄደ።


በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገ​ብም ቃል ኪዳ​ንን አደ​ረጉ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዞት፥ የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮ​ልም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ተመ​ለሱ።


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘ​ቅተ መሐ​ላም መጣ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ለአ​ባቱ ለይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሠዋ።


ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ።


ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።”


ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ።


በሐ​ጸ​ር​ሱ​ዓል፥ በቤ​ር​ሳ​ቤ​ህና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements