Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በፋ​ራን ምድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ እና​ቱም ከም​ድረ ግብፅ ሚስት ወሰ​ደ​ች​ለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በፋራን ምድረ በዳ ሳለም፣ እናቱ ከግብጽ አንዲት ሴት አምጥታ አጋባችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ፥ እናቱም ከምድረ ግብጽ ሚስት ወሰደችለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ፤ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 21:21
18 Cross References  

ድን​ግ​ሊ​ቱን ያገባ መል​ካም አደ​ረገ፤ ያላ​ገባ ግን የም​ት​ሻ​ለ​ውን አደ​ረገ።


ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።


ወጥ​ቶም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ፥ “በቴ​ም​ናታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አይ​ቻ​ለሁ፤ አሁ​ንም እር​ስ​ዋን አጋ​ቡኝ” አላ​ቸው።


ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።


ከዚ​ያም በኋላ ሕዝቡ ከአ​ሴ​ሮት ተጓዙ፤ በፋ​ራ​ንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየ​ጉ​ዞ​አ​ቸው ተጓዙ፤ ደመ​ና​ውም በፋ​ራን ምድረ በዳ ቆመ።


ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”


በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።


ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


አብ​ራ​ምም በከ​ነ​ዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን አጋ​ርን ወስዳ ለአ​ብ​ራም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠ​ችው።


ከም​ድ​ያ​ምም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ከፋ​ራን ሰዎ​ችን ወሰዱ፤ ወደ ግብ​ፅም መጡ፤ ወደ ግብ​ፅም ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን ሄዱ፤ አዴ​ርም ወደ ፈር​ዖን ገባ። እር​ሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረ​ገው።


ኢዮ​አ​ዳም ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አጋ​ባው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጋቡ፤ እነ​ር​ሱም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ይው​ለዱ፤ ከዚ​ያም ተባዙ፤ ጥቂ​ቶ​ችም አት​ሁኑ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements