Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በማግስቱም አብርሃም ማልዶ ተነሣ። ጥቂት ምግብ ወስዶ፣ ውሃ በእርኮት አድርጎ ለአጋር ሰጣት፤ በትከሻዋም አሸክሟት ከነልጇ አሰናበታት። እርሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ትንከራተት ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፥ እርሷም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አብርሃምም ማልዶ ተነሣ እንጀራንም ወሰደ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትክሻው አሸከማት ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት እርስዋም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቀበዘበዘች።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 21:14
28 Cross References  

ባርያ ዘወ​ትር በቤት አይ​ኖ​ርም፤ ልጅ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ ነውና።


ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ።


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ።


አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት።


የሐ​ሴ​ቦን እር​ሻ​ዎ​ችና የሴ​ባማ ወይን ግን​ዶች አዝ​ነ​ዋል። የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች የሰ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች እስከ ኢያ​ዜር ደር​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥ​ተው ነበር፤ ቍጥ​ቋ​ጦ​ቹም ተዘ​ር​ግ​ተው ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረው ነበር።


እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘ​ቅተ መሐ​ላም መጣ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ለአ​ባቱ ለይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሠዋ።


እነ​ሆም፥ በም​ድረ በዳ ሲቅ​በ​ዘ​በዝ ሳለ አንድ ሰው አገ​ኘው፤ ሰው​የ​ውም፥ “ምን ትፈ​ል​ጋ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው።


ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ብላ​ቴ​ኖቹ ተመ​ለሰ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ አብ​ረው ሄዱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተቀ​መጠ።


አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገብ የተ​ምር ዛፍን ተከለ፤ በዚ​ያም የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ።


አብ​ር​ሃ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበ​ረ​በት ስፍራ ለመ​ሄድ ማልዶ ተነሣ፤


የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ልጅ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ዘርህ ነውና።”


ውኃ​ውም ከአ​ቍ​ማ​ዳው አለቀ፤ ሕፃ​ኑ​ንም ከአ​ንድ ቍጥ​ቋጦ ሥር ጥላው ሄደች፤


ያዕ​ቆ​ብም ማልዶ ተነሣ፤ ተን​ተ​ር​ሷት የነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አድ​ርጎ አቆ​ማት፥ በላ​ይ​ዋም ዘይ​ትን አፈ​ሰ​ሰ​ባት።


ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ እር​ሱና እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከሰ​ጢም ተጕ​ዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጡ፤ ሳይ​ሻ​ገ​ሩም በዚያ አደሩ።


ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ገ​ና​ኘት በጥ​ዋት ገሥ​ግሦ ሄደ። ለሳ​ሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ መጣ፤ እነ​ሆም፥ ለራሱ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገ​ሩት። ሳሙ​ኤ​ልም ሰረ​ገ​ላ​ውን መልሶ ወደ ጌል​ጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ከአ​መ​ጣ​ውም ከአ​ማ​ረው ከም​ር​ኮው መንጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሲሠዋ አገ​ኘው፤


ንጉ​ሡም ሕዝ​ቅ​ያስ ማልዶ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት አለ​ቆች ሰበ​ሰበ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ወጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements