Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሣራም አብ​ር​ሃ​ምን አለ​ችው፥ “ይህ​ችን ባሪያ ከነ​ል​ጅዋ አባ​ር​ራት፤ የዚ​ህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አብርሃምንም፣ “ይህችን ባሪያ ከነልጇ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ፣ ከልጄ ከይሥሐቅ ጋራ አይወርስምና” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አብርሃምንም “ይህችን ባርያ ከነልጇ አባርራት፥ የዚህች ባርያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና” አለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሣራም አብርሃምን “ይህችን አገልጋይ ከነልጅዋ ወዲያ አባርልኝ፤ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አብርህምንም፤ ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና አለችው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 21:10
17 Cross References  

ባርያ ዘወ​ትር በቤት አይ​ኖ​ርም፤ ልጅ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


እን​ኪ​ያስ እና​ንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ ልጆች ከሆ​ና​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ናችሁ።


መው​ረስ የኦ​ሪ​ትን ሕግ በመ​ሥ​ራት ከሆነ እን​ግ​ዲህ በሰ​ጠው ተስፋ አይ​ደ​ለማ፤ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ውን ሰጠው።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ሐቅ ትው​ል​ድም ይህ ነው፤ አብ​ር​ሃም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፥


አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው።


አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ።


አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።


ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስ​ትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ይስ​ሐቅ ብለህ ትጠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ በኋላ ለዘሩ አም​ላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳ​ኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ከእ​ርሱ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።


ነፍሰ ገዳይን ከጉባኤ አውጣ፥ ከእርሱም ጋር ክርክር ይወጣል፥ በጉባኤ በሚቀመጥበት ጊዜ ሁሉን ያዋርዳልና።


የገ​ለ​ዓ​ድም ሚስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወለ​ደ​ች​ለት፤ ልጆ​ች​ዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍ​ታ​ሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአ​ባ​ታ​ችን ቤት አት​ወ​ር​ስም” ብለው አስ​ወ​ጡት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements