Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 20:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሣራ​ንም አላት “እነሆ፥ ለወ​ን​ድ​ምሽ አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብር ሰጠ​ሁት፤ ይህም ለፊ​ትሽ ክብር ይሁ​ንሽ፤ በሁ​ሉም እው​ነ​ትን ተና​ገ​ራት።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሣራንም፣ “እነሆ፤ ለወንድምሽ ለአብርሃም አንድ ሺሕ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ፤ ይህም በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና ዐብረውሽ ያሉ ሁሉ እንዲያውቁት ነው፤ በዚህም ንጽሕናሽ ይረጋገጣል” አላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት፥ ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዐይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ፥ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሣራንም “አንቺ ምንም አስነዋሪ ተግባር ያልፈጸምሽ ንጹሕ መሆንሽን ከአንቺ ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲረዱት ምልክት ይሆን ዘንድ ለወንድምሽ ለአብርሃም አንድ ሺህ ብር ሰጥቼዋለሁ” አላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሣራንም አላት እነሆ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 20:16
11 Cross References  

እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።”


ሎሌ​ው​ንም፥ “ሊቀ​በ​ለን በሜዳ የሚ​መጣ ይህ ሰው ማነው?” አለ​ችው። ሎሌ​ውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እር​ስ​ዋም ቀጸ​ላ​ዋን ወስዳ ተከ​ና​ነ​በች።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


የመ​ር​ከ​ቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝ​ተ​ሃል? እን​ዳ​ን​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነን ዘንድ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ክ​ህን ጥራ” አለው።


ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ይህን ሰው፥ ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ነካ ፍርዱ ክፉ ሞት ነው” ብሎ አዘዘ።


አብ​ር​ሃ​ምም ወደ እግ​ዚ​ዘ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ፈወ​ሳ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወለዱ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements