ዘፍጥረት 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 አብርሃምም አለ፥ “ምንአልባት በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት ስለሌለ በሚስቴ ምክንያት ይገድሉኛል ብዬ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 አብርሃምም አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ ‘እዚህ ቦታ ፈሪሀ እግዚአብሔር አለመኖሩን ተገነዘብሁ፤ ሰዎቹም ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል’ ብዬ ሠጋሁ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 አብርሃምም አለ፦ “በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 አብርሃምም አለ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንድሌለ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። See the chapter |