Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የአ​ን​ደ​ኛው ወንዝ ስም ኤፌ​ሶን ነው፤ እር​ሱም ወርቅ የሚ​ገ​ኝ​በ​ትን የኤ​ው​ላጥ ምድ​ርን ይከ​ብ​ባል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፥ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የሐዊላን ምድር ይከብባል፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የመጀመሪያው ወንዝ ፊሶን ይባላል፤ እርሱም ወርቅ በሚገኝበት ሐዊላ በሚባለው ምድር ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የአንደኚው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 2:11
9 Cross References  

ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


ሳኦ​ልም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከኤ​ው​ላጥ ጀምሮ በግ​ብፅ ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ሱር ድረስ መታ​ቸው።


አፌ​ር​ንም፥ ኤው​ላ​ጥ​ንም፥ ዮባ​ብ​ንም ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ናቸው።


የኩ​ሽም ልጆች ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበ​ቅታ ናቸው። የሬ​ጌም ልጆ​ችም ሳባ፥ ዮድ​ዳን ናቸው።


የዚ​ያ​ችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው።


በዚ​ያም የሚ​ያ​በራ ዕን​ቍና የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ አለ። የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እር​ሱም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምድር ሁሉ ይከ​ብ​ባል፤


ኦፌ​ርን፥ ሄው​ላን፥ ኦራ​ምን፥ ዑካ​ብን ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ነበሩ።


“በእ​ው​ነቱ ብር የሚ​ወ​ጣ​በት ቦታ አለ፥ ወር​ቅም የሚ​ነ​ጠ​ር​በት ስፍራ አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements