Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ ሣራ “እኔ አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ጌታዬ አብርሃምም ካረጀ በኋላ እንዲህ ያለ ደስታ ሊኖረኝ ይችላልን?” ብላ በማሰብ ሳቀች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 18:12
12 Cross References  

እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።


አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና።


እን​ግ​ዲ​ያስ እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ እን​ዲሁ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን እንደ ራሳ​ችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባል​ዋን ትፍ​ራው።


በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ መጠ​ጊ​ያ​ችን ነው።


ሴቲ​ቱም ማለዳ መጣች፤ ጌታ​ዋም ባለ​በት በሰ​ው​ዬው ቤት ደጅ ወድቃ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ በዚያ ቀረች።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታ​ቀ​ፊ​ያ​ለሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “አይ​ደ​ለም ጌታዬ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አትዋ​ሻት” አለ​ችው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements