Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፍጥረት 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አንተ፦ አብ​ራ​ምን ባለ​ጠጋ አደ​ረ​ግ​ሁት እን​ዳ​ትል፥ ከአ​ንተ ገን​ዘብ ሁሉ ፈት​ልም ቢሆን፥ የጫማ ማዘ​ቢ​ያም ቢሆን እን​ዳ​ል​ወ​ስድ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ‘አብራምን አበለጸግሁት’ እንዳትል፣ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አንዳች አልፈልግም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23-24 አንተ፦ አብራምን ባለ ጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፥ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አንተ ‘አብራምን ሀብታም ያደረግኹት እኔ ነኝ’ እንዳትል ሌላው ቀርቶ አንዲት ክር ወይም የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አልወስድም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አንተ፤ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥

See the chapter Copy




ዘፍጥረት 14:23
8 Cross References  

ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።


ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።


እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤


የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶር​ያ​ዊ​ውን ይህን ንዕ​ማ​ንን ማረው፤ ካመ​ጣ​ለ​ትም ነገር ምንም አል​ተ​ቀ​በ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በስ​ተ​ኋ​ላው እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች እወ​ስ​ዳ​ለሁ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ንጉ​ሡን፥ “የቤ​ት​ህን እኩ​ሌታ እን​ኳን ብት​ሰ​ጠኝ ከአ​ንተ ጋር አል​ገ​ባም፤ በዚ​ህም ስፍራ እን​ጀ​ራን አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤


ከእኔ በኋላ የሚ​መ​ጣው፥ ከእኔ በፊት የነ​በ​ረው፥ የጫ​ማ​ውን ጠፍር ልፈታ እንኳ የማ​ይ​ገ​ባኝ ነው።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements